6.  የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር ተግባርና ኃላፊነት

ግብርናን ማዕከል ያደረገው የገጠር ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂያችን ተልዕኮ በዋናነት ግብዓትን፣ ምርትን፣ ግብይትን፣ ምርምርንና ኤክሰቴንሽንን በማቀናጀት በክፍለ-አኮኖሚው ዘላቂነት ያለው ሽግግር ማምጣት ሲሆን ራዕዩንና ተልዕኮዉም በአግባቡ ለቋፈፀም የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች እንዲኖሩት ተደርጓል፡፡

·         ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የግብርናና የገጠር ልማት እንዲስፋፋ ያደርጋል፤

·         የመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር ፖሊሲና የደንና የዱር እንስሳት ጥበቃና አጠቃቀም ሕጎችን ያዘጋጃል፤ አፈጻጸማቸውንም ይከታተላል፣ ያስተባብራል፤

·         የምግብ ዋስትና ፕሮግራምን ይመራል፣ ያስተባብራል፤

·         ለገበሬ­ ለአርብቶአደሮች የሚሰጡ የኤክስቴንሽን አገልግሎቶች እንዲስፋፉ ያበረታታል፣ ድጋፍ ይሰጣል፤

·         የውሃ እቀባና አነስተኛ የመስኖ ልማት ሥራ­ እንዲስፋፉ ያበረታታል፣ ድጋፍ ይሰጣል፤

·         ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የገጠር መሠረተ ልማት አገልግሎቶች እንዲስፋፉ ሁኔታ­ ያመቻቻል፤

·         አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር የብድር አገልግሎቶች ለገበሬ­ ለአርበቶአደሮች የሚቀርቡበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤

·         በግብርና መስክ ለተሠማሩ የግል ባለሀብቶች የተሟላ ድጋፍ ይሰጣል፤

·         በግብርና ልማት ላይ ተፅአኖ የሚኖራቸውን ወቅታዊ ሁኔታ­ ይከታተላል፤ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ሥርዓት ይዘረጋል፤

·         ወደ ሀገር በሚገቡትም ሆነ ከሀገር በሚወጡ ዕፅዋት፣ አዝርዕት፣ እንስሳትና የእንስሳት ተዋፅኦ ላይ ተገቢውን የኳራንቲን ቁጥጥር ያደርጋል፤

·         የእስሳትና የዕፅዋት በሽታ­ ወረርሽኝንና ተዛማች ተባዮችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፤

የግብርና ልማት በገበያ እንዲመራና ቀልጣፋ የግብርና ግብዓትና ምርት ግብይት ሥርዓት እንዲፈጠር ለማድረግ፤

o        ገበሬ­ችአርብቶአደሮችና በግብርና ልማት የተሠማሩ ባለሀብቶች በዋጋና በጥራት ተወዳዳሪ ሊሆኑባቸው የሚችሉ ምርቶችን መለየት እንዲችሉ የገበያ ሁኔታ­ችበተለይም የዓለም ገበያን በቅርብ እየተከታተለ የተሟላ፣ ወቅታዊና ትክክለኛ የገበያ መረጃ እንዲያኙ ያደርጋል፤

o        የዋና ዋና የግብርና ምርቶችና ግብዓቶች የገበያ ፍላጎት ትንበያ ጥናት ያካሂዳል፤ ውጤቱንም ለሚመለከታቸው ያሰራጫል፤

o        ለግብርና ግብዓት ግምገማና ማጽደቅ የሚረዱ መመሪያ­ችን የአሠራር ሥርዓቶችን ያወጣል፤ ሥራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል፤

o        የግብርና ግብዓት ጥራቱ ተጠብቆ ለተጠቃሚው መሰራጨቱን ያረጋግጣል፤

o        የግብርና ግብዓት ምርትን፣ አቅርቦትን፣ ሥርጭትንና ግብይትን አቅም ለመገንባት አስፈላጊውን እገዛ ያደርጋል፤

o        የግብርና ምርቶች ገበያ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚስፋፋበትን መንገድ ይቀይሳል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፤

o        ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የግብርና ምርቶች ገበያ ማዕከላት እንዲፈጠሩና እንዲጠናከሩ ሁኔታ­ ያመቻቻል፤

o        የግብርና ምርቶች የጥራት ደረጃቸው ተለይቶ ለገበያ የሚቀርቡበት ሥርዓት እንዲኖር ለማድረግ ከኢትዮጵያ የጥራትና የደረጃ­ ባለሥልጣን ጋር ይተባበራል፤